ቀጥታ፡

ደቡብ አፍሪካ ከዓለም ዋንጫ ተሰናበተች

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 21/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የ32 ዙር ጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ መርሐ ግብር ካናዳ ደቡብ አፍሪካን 1 ለ 0 አሸንፋለች።

በሎስ አንጀለስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ስቴፈን ኢውስታኪዮ በ92ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።

ደቡብ አፍሪካ በኳስ ቁጥጥር ብልጫ ብትወስድም ካናዳ የተሻሉ የግብ እድሎችን ፈጥራለች።

ውጤቱን ተከትሎ  ካናዳ 16 ውስጥ የገባች የመጀመሪያ ሀገር ሆናለች።

ካናዳ በቀጣዩ ዙር ከኔዘርላንድስ እና ሞሮኮ አሸናፊ ጋር ትጫወታለች።

የሰሜን አሜሪካዋ ሀገር በመልካም ግስጋሴዋ ቀጥላለች።

ደቡብ አፍሪካ ከውድድሩ ተሰናብታለች።

ካናዳ እና ደቡብ አፍሪካ ጥሎ ማለፍ ሲገቡ በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

በዓለም ዋንጫው ለመጀመሪያ ጊዜ 48 ሀገራት መሳተፋቸውን ተከትሎ የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) የ32 ዙር የጥሎ ማለፍ መርሐ ግብር ተግባራዊ አድርጓል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም