ሻምፒዮኑ ሲዳማ ቡና ድል ቀንቶታል - ኢዜአ አማርኛ
ሻምፒዮኑ ሲዳማ ቡና ድል ቀንቶታል
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 21/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ37ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና ባህር ዳር ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሀብታሙ ታደሰ በ29ኛው ደቂቃ ግቡን ከመረብ ላይ አሳርፏል።
በሊጉ 19ኛ ድሉን ያስመዘገበው ሻምፒዮኑ ሲዳማ ቡና ነጥቡን ወደ 68 ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ስምንተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ባህር ዳር ከተማ በ47 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ባህር ዳር ከተማ ባለፉት አምስት የሊግ ጨዋታዎች ድል አልቀናውም።