ወላይታ ድቻ ድል ቀንቶታል - ኢዜአ አማርኛ
ወላይታ ድቻ ድል ቀንቶታል
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 21/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 37ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ወላይታ ድቻ አዳማ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ያሬድ ዳርዛ እና ካርሎስ ዳምጠው ግቦቹን አስቆጥረዋል።
በሊጉ 11ኛ ድሉን ያስመዘገበው ወላይታ ድቻ በ50 ነጥብ ደረጃውን ከ9ኛ ወደ 6ኛ ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 12ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዳማ ከተማ በ43 ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዟል።
የመውረድ አጣብቂኝ ውስጥ የገባው አዳማ ከተማ በሊጉ ለመቆየት በመጨረሻ ሳምንት ሃዋሳ ከተማን ማሸነፍ ይኖርበታል።
የዛሬው የሁለቱ ቡድኖች መርሐ ግብር በከባድ ዝናብ ምክንያት ከትናንት ወደ ዛሬ የተዘዋወረ ጨዋታ ነው።