የሱማሌ ክልል ከለውጡ ወዲህ ያስመዘገበው ሁለንተናዊ የልማት ውጤት ሌሎች ክልሎችም በተሞክሮነት ሊወስዱት የሚገባ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የሱማሌ ክልል ከለውጡ ወዲህ ያስመዘገበው ሁለንተናዊ የልማት ውጤት ሌሎች ክልሎችም በተሞክሮነት ሊወስዱት የሚገባ ነው
አዲስ አበባ፤ሰኔ 21/2018 (ኢዜአ):-የሱማሌ ክልል ከለውጡ ወዲህ በአጭር ጊዜ ያስመዘገበው ሁለንተናዊ የልማት ውጤት ሌሎች ክልሎችም በትልቅ ተሞክሮነት ሊወስዱት የሚገባ መሆኑን በብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር) ገለጹ።
ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር) ከሱማሌ ክልል ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ከለውጡ በፊት በነበረው አግላይ የፖለቲካ ስርዓት የሱማሌ ክልል ከመሀል ፖለቲካ በመገለል የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ሳይሆን ቆይቷል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ለውጥ የፈጠረው አካታችና አሳታፊ የፖለቲካ ምኅዳርም የሱማሌ ክልል ህዝብ ከነበረበት የሰላምና የልማት እጦት ተላቆ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነቱን የሚያረጋግጥበት ዕድል መፈጠሩን ገልጸዋል።
የሱማሌ ክልል ህዝብ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ ከሰላምና የልማት እጦት ተላቆ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነቱን እያረጋገጠ መሆኑን ገልጸዋል።
የሱማሌ ክልል የመሰረተ ልማት ማስፋፊያና የግብርና ልማት ሥራዎችም በሀገራዊና ክልላዊ የልማት ዘርፎች ተጨባጭ ውጤቶች እያስመዘገቡ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በሱማሌ ክልል የተመዘገቡ የግብርና እና የመሰረተ ልማት ግንባታ ስኬቶች ክልሉን በአጭር ጊዜ ውስጥ የብልፅግና ተምሳሌት እያደረጉት መሆኑን ተናግረዋል።
የጅግጅጋ ከተማ በፈጣን የልማትና የዕድገት ግስጋሴ ላይ ትገኛለች ያሉት ኃላፊው፤ ከተማዋም ከሀገር አልፎ ቀጣናዊ ኮንፈረንሶችን በማስተናገድ የቱሪዝም ማዕከል የሆነችበትን አቅም መፍጠሯን ገልጸዋል።
የሱማሌ ክልል ከለውጡ ወዲህ በአጭር ጊዜ ያስመዘገበው ሁለንተናዊ የልማት ውጤት ሌሎች ክልሎችም በትልቅ ተሞክሮነት ሊወስዱት የሚገባ መሆኑን ጭምር አስገንዝበዋል።
በቀጣይ የክልሉን የለውጥ ጉዞ አጠናክሮ ለማስቀጠል በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አንስተዋል።