ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ ምርጥ የአየር ጭነት አጓጓዥ አየር መንገድ ሽልማትን አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ሰኔ 21/2018 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ ምርጥ የአየር ጭነት አጓጓዥ አየር መንገድ ሽልማትን አሸንፏል።

አየር መንገዱ ሽልማቱን ያገኘው የኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት በ2026ቱ የእስያ ጭነት፣ ሎጂስቲክስ እና አቅርቦት ሰንሰለት የሽልማት ስነ ስርዓት ላይ ነው።

በዚህም የአፍሪካ ምርጥ የአየር ጭነት አጓጓዥ አየር መንገድ በመባል ተሸላሚ ሆኗል።


 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን በጠበቁ መሰረተ ልማቶች፣ ስልታዊ ጥምረቶች፣እንዲሁም አዳዲስ የሎጂስቲክስ አሰራሮች በመታገዝ ዓለም አቀፍ የሎጂስቲክስ እና የንግድ ግንኙነቶችን በማጠናከር ላይ እንደሚገኝም ገልጿል።

አየር መንገዱ የካርጎ ሽልማቱን ያገኘው በዘርፉ ባለድርሻ አካላትና በደንበኞች በተሰጠ ከፍተኛ ድምፅ መሆኑን አመልክቷል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይህ ስኬት ዕውን እንዲሆን ላስቻሉ አጋሮች፣ደንበኞች እንዲሁም ሰራተኞች ምስጋና አቅርቧል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም