ቀጥታ፡

ክሮሺያ ለጥሎ ማለፍ አለፈች

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 20/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የምድብ 12 የመጨረሻ ጨዋታዎች ከእኩለ ሌሊት በኋላ ተደርገዋል።

በፊላደልፊያ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ክሮሺያ ጋናን 2 ለ 1 አሸንፋለች።

ፔታር ሱሲች እና ኒኮላ ቭላሲች ግቦቹን ለክሮሺያ አስቆጥረዋል።

ዴሪክ ላክሰን የጋናን ብቸኛ ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ውጤቱን ተከትሎ ክሮሺያ በስድስት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ወደ ጥሎ ማለፉ ገብታለች።

አስቀድማ ጥሎ ማለፍ መግባቷን ያረጋገጠችው ጋና በአራት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

በዚሁ ምድብ በኒው ዮርክ ኒው ጀርዚ ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው የምድቡ ጨዋታ እንግሊዝ ፓናማን 2 ለ 0 አሸንፋለች።

ጁድ ቤሊንግሃም እና ሃሪ ኬን ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ወደ ጥሎ ማለፉ ቀድማ የገባችው እንግሊዝ በሰባት ነጥብ የምድቡ መሪ ሆና አጠናቃለች።

ሶስቱንም የምድብ ጨዋታ የተሸነፈችው ፓናማ ያለ ምንም ነጥብ አራተኛ ደረጃን በመያዝ ከውድድሩ ተሰናብታለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም