ቀጥታ፡

የመውረድ ስጋት ያለባቸው ክለቦች የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ይጠበቃሉ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 20/2018 (ኢዜአ)፦  በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ37ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ውሎ ሶስት ጨዋታዎች ይከናወናሉ።

ምሽት 12 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ መድን ከምድረ ገነት ሽሬ  በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ኢትዮጵያ መድን በ46 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል። ተጋጣሚው ምድረ ገነት ሽሬ በበኩሉ በ38 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

በ36ኛ ሳምንት በመቻል 1 ለ 0 የተሸነፈው ኢትዮጵያ መድን ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታል።

መድን የባለፈው ዓመት የሊጉ አሸናፊ እንደነበር ይታወቃል።

ባለፉት አራት ጨዋታዎች ከድል የራቀው ምድረ ገነት ሽሬ ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ ግዴታው ነው።

በሌላኛው መርሐ ግብር ሀዲያ ሆሳዕና ከድሬዳዋ ከተማ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታሉ።

ሀዲያ ሆሳዕና በ43 ነጥብ 1ኛ 3ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ድሬዳዋ ከተማ በ38 ነጥብ 18ኛ ደረጃን በመያዝ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

በ36ኛ ሳምንት ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 1 ለ 0 ያሸነፈው ሀዲያ ሆሳዕና ካሸነፈ በሊጉ መቆየቱን ያረጋግጣል።

በተመሳሳይ በ36ኛ ሳምንት ሸገር ከተማን 2 ለ 0 ያሸነፈው ድሬዳዋ ከተማ ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት ከጨዋታው ሶስት ነጥብ ማግኘት ይጠበቅበታል።

ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አዳማ ከተማ ከወላይታ ድቻ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያከናውናሉ።

አዳማ ከተማ በ43 ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዛል። ወላይታ ድቻ በ47 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በ36ኛ ሳምንት ከመቀሌ 70 እንደርታ ጋር ያለ ግብ አቻ የተለያየው አዳማ ከተማ ዛሬ ካሸነፈ በሊጉ መቆየቱን ያረጋግጣል።

በተመሳሳይ በ36ኛ ሳምንት በኢትዮ ኤሌክትሪክ የ2 ለ 1 ሽንፈት ያስተናገደው ወላይታ ድቻ ወደ አሸናፊነት መንገድ ለመመለስ ይፋለማል።

የዛሬ ጨዋታዎች ላለመውረድ በሚደረገው ትግል ትልቅ ትርጉም የሚሰጣቸው ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም