ቀጥታ፡

ኬፕቨርዴ ለጥሎ ማለፍ አለፈች


አዲስ አበባ፤ ሰኔ 20/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የምድብ ዘጠኝ ጨዋታዎች ከእኩለ ሌሊት በኋላ ተደርገዋል።

በሂውስተን ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኬፕቨርዴ እና ሳዑዲ አረቢያ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

ጨዋታው ተመጣጣኝ ፉክክር ታይቶበታል።

የኬፕቨርዴው ዴሮይ ዱአርቴ የጨዋታው ኮከብ በመባል ተመርጧል።

ውጤቱን ተከትሎ አፍሪካዋቷ ኬፕቨርዴ በሶስት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ በመጀመሪያ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎዋ ጥሎ ማለፉን ተቀላቅላለች።

ኬፕቨርዴ ምንም ሽንፈት እስከ አሁን አላስተናገደችም።

ሳዑዲ አረቢያ በሁለት ነጥብ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ በመያዝ ከውድድሩ ተሰናብታለች።

በዚሁ ምድብ በጓድላሃራ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ስፔን ኡራጓይን 1 ለ 0 አሸንፋለች።

አሌክስ ባኤና በ42ኛው ደቂቃ ግቧን አስቆጥሯል።

የኡራጓዩ ኦግስቲን ካኖቢዮ በ94ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

ይህም በዓለም ዋንጫው የተመዘዘ 10ኛው ቀይ ካርድ ሆኖ ተመዝግቧል።

ስፔን በሰባት ነጥብ የምድብ ስምንት መሪ ሆና በማጠናቀቅ ወደ ጥሎ ማለፉ ገብታለች።

ኡራጓይ በሁለት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ከውድድሩ ተሰናብታለች።

የደቡብ አሜሪካዋ ሀገር ለሁለት ተከታታይ የዓለም ዋንጫዎች ከምድቡ ተሰናብታለች።

የምድብ ስምንት ስምንት እና ዘጠኝ ውጤቶችን ተከትሎ ጋና፣ ግብጽ፣ እንግሊዝ፣ ፖርቹጋል እና ፓራጓይ ወደ ጥሎ ማለፉ መግባታቸውን አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም