ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ወሳኝ ድል ተቀዳጅቷል - ኢዜአ አማርኛ
ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ወሳኝ ድል ተቀዳጅቷል
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 19/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ37ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ አርባምንጭ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሰመረ ሀፍታይ በሰባተኛው ደቂቃ ግቧን ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ከሶሶት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ45 ነጥብ ደረጃውን ከ16ኛ ወደ 14ኛ ከፍ አድርጓል።
በውድድር ዓመቱ 10ኛ ድሉን ያስመዘገበው ወልዋሎ በሊጉ የመቆየት እድሉን ይበልጥ አስፍቷል።
በአንጻሩ በሊጉ 16ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አርባምንጭ ከተማ በ35 ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃ ይዟል።
አርባምንጫ ከተማ ከሊጉ መውረዱ ይታወቃል።
ዛሬ ቀን ላይ በተደረጉ የ37ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ቡና መቀሌ 70 እንደርታን 3 ለ 0 አሸንፏል።
ይህን ተከትሎም መቀሌ 70 እንደርታ ከአርባምንጭ ከተማ በመቀጠል ወደ ከፍተኛ ሊግ የወረደ ሁለተኛ ቡድን ሆኗል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ ፋሲል ከነማን 1 ለ 0፣ ነገሌ አርሲ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 2 ለ 0 አሸንፈዋል።