ቀጥታ፡

መቀሌ 70 እንደርታ ከፕሪሚየር ሊጉ መውረዱ ተረጋገጠ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 19/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 37ኛ ሳምንት ኢትዮጵያ ቡና መቀሌ 70 እንደርታን 3 ለ 0 ረትቷል።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቢንያም ጌታቸው ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ናይጄሪያዊው ዲቫይን ንዋቹኩ (ፍጹም ቅጣት ምት) ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

በውድድር ዓመቱ 14ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው መቀሌ 70 እንደርታ አንድ ጨዋታ እየቀረው በ37 ነጥብ 19ኛ ደረጃን በመያዝ ወደ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ወርዷል።




ከአርባምንጭ ከተማ ቀጥሎ ከሊጉ የወረደ ሁለተኛ ክለብ ሆኗል።

ከፕሪሚየር ሊጉ አራት ክለቦች ይወርዳሉ።

በሊጉ 13ኛ ድሉን ያስመዘገበው ኢትዮጵያ ቡና በ50 ነጥብ ደረጃውን ከ10ኛ ወደ 7ኛ ከፍ አድርጓል። ቡናማዎቹ ከሶስት የሊጉ ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸፊነት ተመልሰዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም