ቅዱስ ጊዮርጊስ ፋሲል ከነማን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ አራተኛ ከፍ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
ቅዱስ ጊዮርጊስ ፋሲል ከነማን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ አራተኛ ከፍ አደረገ
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 19/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ37ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ፋሲል ከነማን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፍጹም ጥላሁን በ24ኛው ደቂቃ ግቧን አስቆጥሯል።
በሊጉ 14ኛ ድሉን ያስመዘገበው ቅዱስ ጊዮርጊስ በ53 ነጥብ ደረጃውን ከስድስተኛ ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 11ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ፋሲል ከነማ በ52 ነጥብ ከነበረበት አራተኛ ደረጃ ወደ አምስተኛ ዝቅ ብሏል።