ነገሌ አርሲ ድል ቀንቶታል - ኢዜአ አማርኛ
ነገሌ አርሲ ድል ቀንቶታል
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 19/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 37ኛ ሳምንት የመጀመሪያ መርሐ ግብር ነገሌ አርሲ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ በረከት ወልዴ (ፍጹም ቅጣት ምት) እና ሀቢብ ከማል ግቦቹን አስቆጥረዋል።
በሊጉ 15ኛ ድሉን ያስመዘገበው ነገሌ አርሲ በ60 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።
ዘንድሮ በፕሪሚየር ሊጉ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተሳተፈ የሚገኘው ነገሌ አርሲ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ የማጠናቀቅ እድሉን የበለጠ አስፍቷል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 13ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ46 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ንግድ ባንክ ባለፉት ሁለት የሊግ ጨዋታዎች ሽንፈት አስተናግዷል።