ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ከፓኪስታን ጋር ያላትን አጋርነት ይበልጥ ለማሳደግ ትሰራለች-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 19/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ከፓኪስታን ጋር ያላትን የሁለትዮሽ አጋርነት ለማጠናከር እንደምትሰራ አስታወቁ።

የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሼህባዝ ሸሪፍ በ7ኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ላሸነፈውና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሚመራው ብልፅግና ፓርቲ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሼህባዝ ሸሪፍ በሰጡት ምላሽ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዘላቂ የወንድማማችነት መንፈስ የሚያንጸባርቅ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ እና ፓኪስታን በለውጥና በጽናት እየተጓዙ ያሉ ሀገራት መሆናቸውን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለብልጽግና እና ለዕድገት ያላቸው ቁርጠኝነት ይበልጥ እንደሚያስተሳስራቸው አመልክተዋል።

ሁለቱ ሀገራት በገቡት የጋራ ቃል ኪዳን መሠረት፣ በቀጣይ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር እና አጋርነታቸውን ወደ ላቀ ምዕራፍ ለማሸጋገር እንደሚሰሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም