የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር በማር ምርት ላይ ተጨባጭ ውጤቶችን እያስገኘ ነው- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር በማር ምርት ላይ ተጨባጭ ውጤቶችን እያስገኘ ነው- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 18/2018 (ኢዜአ):- የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር በማር ምርት ላይ ተጨባጭ ውጤቶችን እያስመዘገበ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው፤ አረንጓዴ ዐሻራ ለአየር ንብረት ጥበቃ ከሚያበረክተው መሠረታዊ አስተዋፅዖ ባለፈ፣ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የማር ምርት ላይ ተጨባጭ ውጤቶችን እያስመዘገበ እንደሚገኝ አመልክተዋል።
ተፈጥሮንና አካባቢያችንን በመጠበቃችን፣ ደኖች እየተስፋፉ በመምጣታቸው፣ የንብ ዝርያዎችን የሚያግዙና የማር ምርትን የሚያሳድጉ ምቹ ከባቢዎች ምክንያት የምግብ ምንጮች ሊፈጠሩ መቻላቸውን ተናግረዋል።
ተስፋን እንትከል! ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።