ቀጥታ፡

እያደገ የመጣው የኢትዮጵያ ዓለም አቀፋዊ ተሰሚነት ይበልጥ የተረጋገጠው፣ የኮፕ32 ጉባኤን እንድታስተናግድ በመመረጧ ነው

አዲስ አበባ፤ሰኔ 16/2018 (ኢዜአ)፦እያደገ የመጣው የኢትዮጵያ ዓለም አቀፋዊ ተሰሚነት ይበልጥ የተረጋገጠው፣ የኮፕ32 ጉባኤን እንድታስተናግድ በመመረጧ መሆኑን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በምክትል ዋና ጸሐፊ ማዕረግ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክላቨር ጋቴቴ ገለጹ፡፡

‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት “ከለውጥ ወደ ዘላቂ ሽግግር” በሚል መሪ ቃል የ“ኢትዮጵያ ታከናውናለች” ጉባኤ በመካሄድ ላይ ነው።

‎’ኢትዮጵያ ታከናውናለች’ ብሔራዊ ጉባኤ ላይ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በምክትል ዋና ጸሐፊ ማዕረግ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ክላቨር ጋቴቴ ንግግር አድርገዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃግብርን፣ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ላይ የተመሰረተውን የኃይል ሽግግር፣ በኢ-ሞቢሊቲ የሚመራውን የትራንስፖርት ዘርፍ ለውጥ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድን ቀጣይነት ያለው እድገት በመጥቀስ ኢትዮጵያን በአዎንታዊ የለውጥ ተሞክሮነት አንስተዋል።

እያደገ የመጣውን የኢትዮጵያ ዓለም አቀፋዊ ተሰሚነት ይበልጥ የተረጋገጠው፣ የኮፕ32 ጉባኤን እንድታስተናግድ መመረጧ መሆኑን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ ይህም አፍሪካ ከምላሽ ሰጪነት ባለፈ በንቃት እየመራች መሆኑን የሚያሳይ ትልቅ ማረጋገጫ ነው ብለዋል።

‎‎የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ለኢትዮጵያ የለውጥ ጉዞ እና ለአጠቃላይ የአፍሪካ አጀንዳ ያለውን ሙሉ ድጋፍ በድጋሚ አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም