ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ላይ የቦታ ለውጥ ተደረገ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 16/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።

የሲዳማ ቡና እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ መርሐ ግብር ማክሰኞ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ለማካሄድ ቀን ተቆርጦለት ነበር።

ቀደም ሲል በአዲስ አበባ ስታዲየም ሊካሄድ የነበረው የፍጻሜ ጨዋታ ቀኑ ሳይቀየር የቦታ ለውጥ ተደርጎለት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እንደሚካሄድ ፌዴሬሽኑ አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም