ኢትዮጵያ ያላትን የተፈጥሮ ሀብት አቅም ወደ ተጨባጭ ብሔራዊ ዕድገት እየቀየረች ነው - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ያላትን የተፈጥሮ ሀብት አቅም ወደ ተጨባጭ ብሔራዊ ዕድገት እየቀየረች ነው
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 16/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ያላትን የተፈጥሮ ሀብት አቅም ወደ ተጨባጭ ብሔራዊ ዕድገት እየቀየረች እንደምትገኝ የማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ሐና ብርሃኑ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት “ከለውጥ ወደ ዘላቂ ሽግግር” በሚል መሪ ቃል የ“ኢትዮጵያ ታከናውናለች” ጉባኤ በመካሄድ ላይ ነው።
የማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ሐና ብርሃኑ፣ በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ከነበረበት ደካማ አፈጻጸም ተነስቶ አሁን ላይ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ስትራቴጂካዊ ምሰሶዎች አንዱ መሆን የቻለበትን የማዕድን ትራንስፎርሜሽን ጉዞ አቅርበዋል።
በቁርጠኛ ማሻሻያዎች፣ በገበያ መልሶ ማዋቀር እና እሴትን መጨመር በሚያስችሉ ኢንቨስትመንቶች በመታገዝ ዘርፉ ከፍተኛ የወጪ ንግድ ገቢን እያስገኘ፣ የገቢ ምርቶችን ጥገኝነት እየቀነሰ እና ለኢንዱስትሪ ልማት አዳዲስ ዕድሎችን እየፈጠረ እንደሚገኝ አመልክተዋል።
በወርቅ፣ በወሳኝ ማዕድናት፣ በነዳጅ እና በማዳበሪያ ምርት ላይ እየተስፋፋ በመጣው የኢንቨስትመንት ለውጦች፣ ኢትዮጵያ ያላትን የተፈጥሮ ሀብት አቅም ወደ ተጨባጭ ብሔራዊ ዕድገት እየቀየረችው ትገኛለች ብለዋል።
ሚኒስትር ዴኤታዋ፤ እነዚህ ስኬቶችም በሀገር በቀል ቅኝት የሪፎርም ማሻሻያ፣ በገዘፈ ርዕይ እና አፈጻጸም ድምር ውጤት እንደሚያስገኙ ህያው ማረጋገጫዎች መሆናቸውን ገልጸዋል።