ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ አዲስ የከተማ ልማት ምዕራፍ ውስጥ እየገባች ነው

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 16/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ አዲስ የከተማ ልማት ምዕራፍ ውስጥ እየገባች እንደምትገኝ በገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ትዕግሥት ፍስሀ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት “ከለውጥ ወደ ዘላቂ ሽግግር” በሚል መሪ ቃል የ“ኢትዮጵያ ታከናውናለች” ጉባኤ እየተካሄደ ነው።

በገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ትዕግሥት ፍስሀ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ አዲስ የከተማ ልማት ምዕራፍ ውስጥ እየገባች መሆኑን አመልክተዋል።

የልማቱ ትኩረት ከተሞችን ምቹ፣ ተወዳዳሪ፣ ሁሉን አቀፍና ዘመናዊ ማድረግ ነው ብለዋል።

አማካሪዋ አክለውም ይህም ከተሞች ለሥራ ዕድል ፈጠራና ለጋራ ብልፅግና ቀጣይ ሞተር እንዲሆኑ የማድረግ ውጥን እንዳለውም አብራርተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም