የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያው የሀገር ውስጥ መረጋጋትንና ተዓማኒነትን መልሶ እንዲመጣ አድርጓል- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያው የሀገር ውስጥ መረጋጋትንና ተዓማኒነትን መልሶ እንዲመጣ አድርጓል- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 16/2018 (ኢዜአ)፦የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያው የሀገር ውስጥ መረጋጋትንና ተዓማኒነትን መልሶ ማምጣቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት “ከለውጥ ወደ ዘላቂ ሽግግር” በሚል መሪ ቃል የ“ኢትዮጵያ ታከናውናለች” ጉባኤ እየተካሄደ ነው።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)፤ የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያ የሀገር ውስጥ መረጋጋትንና ተዓማኒነትን መልሶ ማምጣቱን ገልጸዋል።
ይህ ውጤት የተገኘው የዋጋ ንረትን በመቆጣጠር፣ የውጭ ምንዛሪ ገበያውን ነፃ በማድረግ፣ የገንዘብና የፊስካል ፖሊሲን በማዘመን፣ እንዲሁም ለዘላቂና አካታች ዕድገት ጠንካራ መሠረት ለመጣል የፋይናንስ ዘርፉን በማጠናከር መሆኑን አብራርተዋል።