አልጄሪያ በዓለም ዋንጫው የመጀመሪያ ድሏን አስመዘገበች - ኢዜአ አማርኛ
አልጄሪያ በዓለም ዋንጫው የመጀመሪያ ድሏን አስመዘገበች
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 16/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ አልጄሪያ ከመመራት ተነስታ ጆርዳንን 2 ለ 1 አሸንፋለች።
ማለዳ ላይ በሳን ፍራንሲስኮ ቤይ ኤሪያ ስታዲየም በተካሄደው የምድብ 10 ጨዋታ ኒዛር አል ራሽዳን በ36ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ጎል ጆርዳን መሪ ሆናለች።
ከእረፍት መልስ ናዲር ቤንቡአሊ በ69ኛው ደቂቃ አልጄሪያን አቻ ያደረገችውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
አሚን ጎሪ በ82ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ግብ አልጄሪያን ድል እንድትቀዳች አስችሏል።
የሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር የጨዋታ የበላይነት ነበራት።
በውድድሩ የመጀመሪያ ድሏን ያስመዘገበችው አልጄሪያ በሶስት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዛለች። ወደ ጥሎ ማለፉ የመግባት እድሏን አስፍታለች።
ሁለተኛ ሽንፈቷን ያስተናገደችው ጆርዳን ከዓለም ዋንጫው ተሰናብታለች።
ጆርዳን በዓለም ዋንጫው ስትሳተፍ የዘንድሮው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
በዚሁ ምድብ ትናንት ማምሻውን በተደረገ ጨዋታ የወቅቱ የውድድሩ አሸናፊ አርጀንቲና ኦስትሪያን 2 ለ 0 በመርታት ወደ ጥሎ ማለፉ ተሸጋግራለች።
አልጄሪያ ከኦስትሪያ፣ ጆርዳን ከአርጀንቲና በምድብ 10 የሚደረጉ የመጨረሻ ጨዋታዎች ናቸው።