ቀጥታ፡

ሀዲያ ሆሳዕና ወደ አሸናፊነት ተመልሷል

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 15/2018 (ኢዜአ):- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ36ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሀዲያ ሆሳዕና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 1 ለ 0 አሸንፏል።

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ብሩክ በየነ በመጀመሪያ አጋማሽ ማብቂያ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።

ከሶስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ሀዲያ ሆሳዕና በ46 ነጥብ ደረጃውን ከ15ኛ ወደ 13ኛ ከፍ ብሏል።

በሊጉም 11ኛ ድሉን አስመዝግቧል።


በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 12ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ42 ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዟል።

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ባለፉት አራት ጨዋታዎች ድል አልቀናውም።

ዛሬ አስቀድመው በተደረጉ የ36ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ፋሲል ከነማ አርባምንጭ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።

ውጤቱን ተከትሎ አርባምንጭ ከተማ ከሊጉ የወረደ የመጀመሪያ ቡድን ሆኗል።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ወላይታ ድቻን 2 ለ 1 ረቷል።

ጨዋታዎቹን ተከትሎ የ36ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ተጠናቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም