የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ምድረ ገነት ሽሬ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ - ኢዜአ አማርኛ
የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ምድረ ገነት ሽሬ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 15/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 36ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ምድረ ገነት ሽሬ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ትናንት በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እስከ 90ኛው ደቂቃ ተደርጎ በመብራት ምክንያት መቋረጡ ይታወቃል።
የቡድኖቹ ቀሪ ስድስት ደቂቃ ዛሬ ረፋድ ላይ የተካሄደ ሲሆን ጨዋታው ግብ ሳይቆጠርበት በአቻ ውጤት ተጠናቋል።
ከሶስት ተከታታይ ድሎች በኋላ አቻ የወጣው ቅዱስ ጊዮርጊስ በ50 ነጥብ ደረጃውን ከአምስተኛ ወደ አራተኛ ደረጃ ከፍ አድርጓል።
ምድረ ገነት ሽሬ በ39 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
ቡድኑ ባለፉት አራት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።