ቀጥታ፡

በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ በህዝብ በይሁንታ የተሰጠውን ድምፅ እናከብራለን - የወሎ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ

አዲስ አበባ ፤ ሰኔ 15/2018 (ኢዜአ) ፦ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ በህዝብ በይሁንታ የተሰጠውን ድምፅ እናከብራለን ሲል የወሎ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(ወዴፓ) ገለጸ።

ፓርቲው ለኢዜአ በላከው መግለጫ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላም በጠናቀቁ የተሰማውን ደስታ ቀደም ሲል መግለጹን አስታውሶ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተገለጸው ውጤት መሰረትም በህዝብ ይሁንታ የተሰጠውን ድምጽ እንደሚያከብር አስታውቋል።

በቦርዱ መግለጫ መሰረት የብልጽግና ፓርቲ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለከተማና ክልል ምክር ቤቶች መንግስት መመስረት የሚያስችለውን ድምጽ ማግኘቱን በማንሳት ለፓርቲው አመራሮች ፣ለአባላትና ለመራጩ ህዝብ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

በቀጣይ አምስት ዓመታትም ኢትዮጵያ ያሉባት ችግሮች ሙሉ በሙሉ የሚቀረፉበት የጀመረችው ምክክር በውጤት የሚጠናቀቅበት እንደሚሆን ያለውን እምነት ገልጿል።

የሰለጠነ የዲሞክራሲ ስርአት ጅማሮ ላይ ላለችው ሀገራችን የሰላምና የእድገት የመሻገር ጊዜ እንዲሆን እየተመኘን ፓርቲያችን የሀገር ሉአላዊነትን ፣ የልማትና የእድገት ጉዞን የሚያደናቅፉ የውጭም ሆነ የውስጥ የጥፋት ሀይሎችን ከመንግስት ጎን ቆመን የምንታገል መሆኑን እናረጋግጣለን ሲል ፓርቲው መልዕክቱን አስተላልፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም