ኬፕቨርዴ ከኡራጓይ ጋር አቻ ተለያየች - ኢዜአ አማርኛ
ኬፕቨርዴ ከኡራጓይ ጋር አቻ ተለያየች
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 15/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ኬፕቨርዴ እና ኡራጓይ ሁለት አቻ ተለያይተዋል።
ከእኩለ ሌሊት በኋላ በሚያሚ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የምድብ ሰባት ጨዋታ ኬቨን ፒና እና ሄሊዮ ቫሬላ የኬፕቨርዴን ጎሎች አስቆጥረዋል።
ፒና በዓለም ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተሳተፈች ለምትገኘው አፍሪካዊቷ ኬፕቨርዴ በውድድሩ የመጀመሪያ ግቧን በማስቆጠር ታሪክ ሰርቷል።
የደሴቲቷ ሀገር ከስፔን ጋር በመጀመሪያ ጨዋታዋ ያለ ግብ አቻ ተለያይታ የመጀመሪያ ነጥቧን ማግኘቷ የሚታወስ ነው።
ማክሲ አራውጆ እና ኦግስቲን ካኖቢዮ የኡራጓይን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
በጨዋታው ኬፕቨርዴ የግብ እድሎችን በመፍጠር፣ ኡራጓይ በኳስ ቁጥጥር የተሻሉ ነበሩ።
የኬፕቨርዴው ኬቨን ፒና የጨዋታው ኮከብ በመባል ተመርጧል።
ውጤቱን ተከትሎ ኡራጓይ እና ኬፕቨርዴ በተመሳሳይ ሁለት ነጥብ በግብ ልዩነት ተበላልጠው ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።
ትናንት ማምሻውን በምድብ ስምንት በተካሄደ ጨዋታ ስፔን ሳዑዲ አረቢያን 4 ለ 0 በማሸነፍ ምድቡን በአራት ነጥብ እየመራች ነው።
በምድብ ስምንት የመጨረሻ መርሐ ግብር ኬፕቨርዴ ከሳዑዲ አረቢያ እና ኡራጓይ ከስፔን ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።