ግብጽ በዓለም ዋንጫ ተሳትፎ ታሪኳ የመጀመሪያ ድሏን አስመዘገበች - ኢዜአ አማርኛ
ግብጽ በዓለም ዋንጫ ተሳትፎ ታሪኳ የመጀመሪያ ድሏን አስመዘገበች
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 15/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የምድብ ሰባት መርሐ ግብር ግብጽ ከመመራት ተነስታ ኒውዝላንድን 3 ለ 1 አሸንፋለች።
ከእኩለ ሌሊት በኋላ በቢሲ ፕሌስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ትሪዝጌት፣ መሐመድ ሳላህ እና ሙስጠፋ ዚኮ የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።
ፊን ሱርማን ለኒውዝላንድ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ግብጽ በጨዋታው የተሻለ እንቅስቃሴ አድርጋለች።
የግብጹ መሐመድ ሳላህ የጨዋታው ኮከብ ሆኖ ተመርጧል።
በዓለም ዋንጫው ለአራተኛ ጊዜ የተሳፈተፈችው ግብጽ በውድድር ተሳትፎ ታሪኳ የመጀመሪያ ድሏን አስመዝግባለች።
ምድብ ሰባትን በአራት ነጥብ መምራት ጀምራለች።
ኒውዝላንድ በአንድ ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዛለች።
በዚሁ ምድብ ትናንት ማምሻውን በተደረገ ሌላኛው ጨዋታ ቤልጂየም እና ኢራን ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ግብጽ ከኢራን፣ ኒውዝላንድ ከቤልጂየም የምድብ ሰባት የመጨረሻ ጨዋታዎች ናቸው።