ቀጥታ፡

ቤልጂየም እና ኢራን አቻ ተለያዩ


አዲስ አበባ፤ ሰኔ 14/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የምድብ ሰባት መርሐ ግብር ቤልጂየም እና ኢራን ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

ማምሻውን በሎስ አንጀለስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቤልጂየም ከፍተኛ ብልጫ ብትወስድም ግብ ማስቆጠር ተስኗታል።

የተደራጀ መከላከል እና የመልሶ ማጥቃት ስልት ይዞ የገባው የኢራን ብሔራዊ ቡድን ከጨዋታው ወሳኝ ነጥብ አግኝቷል።

የቤልጂየሙ ተከላካይ ናታን ንጎይ በ66ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል።

ይህም በዓለም ዋንጫው የተመዘገበ ስምንተኛው ቀይ ካርድ ሆኗል።

ውጤቱን ተከትሎ ኢራን እና ቤልጂየም በተመሳሳይ ሁለት ነጥብ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃን ይዘዋል።

በዚሁ ምድብ ኒውዝላንድ ከግብጽ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ላይ በቢሲ ፕሌስ ስታዲየም ይጫወታሉ።

ሁለቱም ሀገራት በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታቸው አቻ ተለያይተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም