ቀጥታ፡

መቻል ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 14/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ36ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች ዛሬ ተደርገዋል።

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው ጨዋታ መቻል ኢትዮጵያ መድንን 1 ለ 0 አሸንፏል።

መሐመድ አበራ በ61ኛው ደቂቃ ግቧን አስቆጥሯል።

ውጤቱን ተከትሎ መቻል በ56 ነጥብ ሶስተኛ፣ ኢትዮጵያ መድን በ46 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዘዋል።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ሌላኛው ጨዋታ መቀሌ 70 እንደርታ እና አዳማ ከተማ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

መቀሌ 70 እንደርታ በ37 ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

አዳማ ከተማ በ43 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እየተደረገ የነበረው የምድረ ገነት ሽሬ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ በ90ኛው ደቂቃ መብራት በመጥፋቱ ምክንያት ተቋርጧል።

ጨዋታው እስከተቋረጠበት ጊዜ ግብ አልተቆጠረም።  ቀሪው ስድስት ደቂቃ ነገ ከረፋዱ አራት ሰዓት ላይ እንደሚካሄድ የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል።

በዕለቱ የመጀመሪያ መርሐ ግብር
ሃዋሳ ከተማ እና ባህር ዳር ከተማ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ተካሄዷል።

ውጤቱን ተከትሎ ሃዋሳ ከተማ በ49 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል።

ባህር ዳር ከተማ በ47 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ባህር ዳር ከተማ በሊጉ በበርካታ ጨዋታዎች አቻ የወጣ (20 ጊዜ) የወጣ ቡድን ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም