ስፔን በሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፈች - ኢዜአ አማርኛ
ስፔን በሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፈች
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 14/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የምድብ ስምንት መርሐ ግብር ስፔን ሳዑዲ አረቢያን 4 ለ 0 ረትታለች።
ማምሻውን በአትላንታ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሚኬል ኦያርዛባል (ሁለት)፣ ላሚን ያማል እና የሳዑዲ አረቢያው ሀሰን አል ታምባክቲ በራሱ ላይ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ስፔን በጨዋታው ፍጹም ብልጫ ወስዳለች።
ውጤቱን ተከትሎ ስፔን ምድብ ስምንትን በአራት ነጥብ መምራት ጀምራለች።
ሳዑዲ አረቢያ በአንድ ነጥብ ሶስተኛ ደሰጃን ይዛለች።
በዚሁ ምድብ ኡራጓይ ከአፍሪካዊቷ ኬፕቨርዴ ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ላይ በሚያሚ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታቸው አቻ ተለያይተዋል።