ቀጥታ፡

ብልጽግና ፓርቲ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ አብላጫ ድምጽ አግኝቷል

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 14/2018 (ኢዜአ)፦ ብልጽግና ፓርቲ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ በተሰጠባቸው የምርጫ ክልሎች አብላጫ ድምጽ ማግኘቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

የብሔራዊ የምርጫ ቦርድ አጠቃላይ የ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ውጤት ማሳወቂያ መርሀ ግብር በማካሄድ ላይ ነው።

በመድረኩም የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴን ጨምሮ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ሀይሉ፣ በምርጫው የተሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲ አመራር አባላት፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች እና የሲቪክ ማህበራት፣ የሀገራት አምባሳደሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ተስፋዬ ንዋይ የሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ውጤት በዝርዝር ይፋ አድርገዋል።

በዚሁ መሰረት ብልጽግና ፓርቲ በተወዳደረባቸው የሕዝብ ተወካዮች እና የክልል ምክር ቤቶች አብላጫ ድምፅ ማግኘቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም