ሃዋሳ ከተማ እና ባህር ዳር ከተማ አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ሃዋሳ ከተማ እና ባህር ዳር ከተማ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 14/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ36ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሃዋሳ ከተማ እና ባህር ዳር ከተማ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።
የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ተካሄዷል።
ውጤቱን ተከትሎ ሃዋሳ ከተማ በ49 ነጥብ ደረጃውን ከስድስተኛ ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል። ቡድኑ ባለፉት ተከታታይ ጨዋታዎች አላሸነፈም።
ባህር ዳር ከተማ በ47 ነጥብ ከነበረበት 12ኛ ደረጃ ወደ 9ኛ ከፍ ብሏል። ካለፉት ጨዋታዎች ሶስት ነጥብ ማግኘት አልቻለም።
ባህር ዳር ከተማ በሊጉ በበርካታ ጨዋታዎች አቻ የወጣ (20 ጊዜ) የወጣ ቡድን ነው።