ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮጵያ ቡና ነጥብ ተጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮጵያ ቡና ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 13/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 36ኛ ሳምንት የመጀመሪያ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮጵያ ቡና ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በአዲስ አበባ ስታዲየም ተካሄዷል።
ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ46 ነጥብ ደረጃውን ከ12ኛ ወደ 11ኛ ከፍ አድርጓል። ቡድኑ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ድል አልቀናውም።
ኢትዮጵያ ቡና በበኩሉ በ47 ነጥብ ከነበረበት 11ኛ ደረጃ ወደ 9ኛ ከፍ ብሏል።
ቡናማዎቹ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች ሶስት ነጥብ ማግኘት አልቻሉም።