አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ 1 ሺህ 387 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው - ኢዜአ አማርኛ
አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ 1 ሺህ 387 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 13/2018 (ኢዜአ)፦አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መርኃግብሮች ትምሕርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ የ2018 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው፡፡
በዚህ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትርና የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ መላኩ አለበል፣ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱራህማንን ጨምሮ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች እንዲሁም የተመራቂ ቤተሰቦችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ዩኒቨርሲቲው በዛሬው ዕለት የሚያስመርቃቸው ተማሪዎች በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዲግሪ (PhD) እንዲሁም ሌሎች መርኃግብሮች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 1ሺህ 387 ተመራቂዎች ናቸው፡፡