ቀጥታ፡

ፓራጓይ ወሳኝ ድል ተቀዳጅታለች

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 13/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የምድብ አራት መርሐ ግብር ፓራጓይ ቱርኪዬን 1 ለ 0 አሸንፋለች።

ማለዳ ላይ በሳንፍራንሲስኮ ቤይ ኤሪያ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ማቲያስ ጋላርዛ በ64ኛው ሴኮንድ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።

ጎሉ የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ፈጣን ጎል ሆኖ ተመዝግቧል።

በመጀመሪያው አጋማሽ ማብቂያ የፓራጓይ የአማካይ ተጫዋች ሚጉዌል አልሚሮን በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል።

አልሚሮን አፉን በእጅ ሸፍኖ የተቃራኒ ቡድን ተጫዋች በመናገሩ  ቀይ ካርድ ተመልክቷል።

ይህም የ32 ዓመቱ አማካይ አፍን በእጅ ሸፍኖ መናገር ቀይ ካይ ካርድ የሚያሰጥበት አዲሱ የፊፋ ህግ ተግባራዊ የሆነበት የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል።

ቱርኪዬ ያገኘችውን የቁጥር ብልጫ ተጠቅማ ግብ ማስቆጠር አልቻለችም።

ውጤቱን ተከትሎ ፓራጓይ በሶስት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች።

ሁለተኛ ሽንፈቷን ያስተናገደችው ቱርኪዬ ያለ ምንም ነጥብ አራተኛ ደረጃን በመያዝ ሃይቲን ተከትላ ከውድድሩ የተሰናበተች ሁለተኛ ሀገር ሆናለች።

በዚሁ ምድብ ትናንት ማምሻውን በተደረገ ጨዋታ አሜሪካ አውስራሊያን 2 ለ 0 በማሸነፍ ጥሎ ማለፍ መግባቷን አረጋግጣለች።

ቱርኪዬ ከአሜሪካ፣ ፓራጓይ ከአውስትራሊያ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታዎች ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም