ብራዚል ድል ቀንቷታል - ኢዜአ አማርኛ
ብራዚል ድል ቀንቷታል
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 13/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የምድብ ሶስት ጨዋታ ብራዚል ሃይቲን 3 ለ 0 አሸንፋለች።
ከእኩለ ሌሊት በኋላ በፊላደልፊያ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ማትያስ ኩንሃ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ቪኒሸስ ጁኒየር ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ብራዚል በጨዋታው ፍጹም የበላይነት ወስዳለች።
የብራዚሉ ራፊኒያ ጉዳት አጋጥሞት በመጀመሪያው አጋማሽ ተቀይሮ ወጥቷል።
ቪኒሸስ ጁኒየር የጨዋታው ኮከብ በመባል ተመርጧል።
ውጤቱን ተከትሎ ብራዚል በአራት ነጥብ ምድብ ሶስትን እየመራች ነው።
ሁለተኛ ሽንፈቷን ያስተናገደችው ሃይቲ ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛለች።
በዚሁ ምድብ በተደረገው ሌላኛው ጨዋታ ሞሮኮ ስኮትላንድን 1 ለ 0 በመርታት በአራት ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጣ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች።
ስኮትላንድ በሶስት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
በምድብ አራት የመጨረሻ መርሐ ግብር ሞሮኮ ከሃይቲ እና ስኮትላንድ ከብራዚል ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ጨዋታዎቹ ወደ ጥሎ ማለፍ የሚገቡ አገራትን ይለያሉ።