ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ሰኔ 30 ይካሄዳል

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 12/2018 (ኢዜአ):- የሲዳማ ቡና እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ይከናወናል።

ጨዋታው ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚደረግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

አሸናፊው ቡድን ኢትዮጵያን ወክሎ በቀጣዩ ዓመት በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ላይ ይሳተፋል።

የኢትዮጵያ ዋንጫ ከ1937 ዓ.ም አንስቶ እየተካሄደ የሚገኝ አንጋፋ የክለቦች የጥሎ ማለፍ ውድድር ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም