ደቡብ አፍሪካ ከቼክ ሪፐብሊክ ጋር አቻ ተለያይታለች - ኢዜአ አማርኛ
ደቡብ አፍሪካ ከቼክ ሪፐብሊክ ጋር አቻ ተለያይታለች
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 11/2018 (ኢዜአ):- በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የምድብ አንድ ሁለተኛ መርሐ ግብር ቼክ ሪፐብሊክ እና ደቡብ አፍሪካ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።
ማምሻውን በአትላንታ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ማይክል ሳዲሌክ በስድስተኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ጎል ቼክ ሪፐብሊክን መሪ አድርጓል።
ቴብሆ ሞክዌና በ83ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ባሳረፋት ግብ ደቡብ አፍሪካ አቻ ሆናለች።
በጨዋታው ደቡብ አፍሪካ የተሻለ ብልጫ ነበራት።
ደቡብ አፍሪካ በዓለም ዋንጫው የመጀመሪያ ነጥቧን አግኝታለች። ቼክ ሪፐብሊክም በተመሳሳይ የመጀመሪያ ነጥቧን አሳክታለች።
ደቡብ አፍሪካ ወደ ጥሎ ማለፉ የመግባት ተስፋዋን ለማለምለም በመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋ ኮሪያ ሪፐብሊክን ማሸነፍ ይኖርባታል።
በዚሁ ምድብ ሜክሲኮ ከኮሪያ ሪፐብሊክ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ላይ በጓድላሃራ ስታዲየም ይጫወታሉ።
ሁለቱ ሀገራት የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታቸውን ማሸነፋቸው የሚታወቅ ሲሆን አሸናፊው ቡድን ወደ ጥሎ ማለፍ መግባቱን ያረጋግጣል።