የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት (ካቢኔ) የቀረበለትን የበጀት ክለሳ አፀደቀ - ኢዜአ አማርኛ
የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት (ካቢኔ) የቀረበለትን የበጀት ክለሳ አፀደቀ
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 10/2018 (ኢዜአ) ፦ የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት (ካቢኔ) ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የ2018 የበጀት አመት የ11 ወራት እቅድ አፈጻጸም መነሻ በማድረግ የቀረበለት የበጀት ክለሳ አፅድቋል።
ካቢኔው በክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ አማካኝነት የቀረበለትን ከ301 ሚሊየን 693 ሺህ 178 ብር የበጀት ክለሳ ነው ተወያይቶ ያፀደቀው።
የበጀት ክለሳው በተለይም የፊዚካልና ፋይናንሻል አፈፃፀማቸው ዝቅተኛ የሆኑ ፕሮጀክቶችን በመለየት የላቀ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳ ላላቸውና የበጀት እጥረት ላጋጠማቸው ጉዳዮች የሚውል ነው ተብሏል።
አፈፃፀማቸው ዝቅተኛ የሆኑ ፕሮጀክቶችን በመለየትና በመከለስ የቅድሚያ ቅድሚያ ለተሰጣቸው ተግባራት በቀሪው የበጀት ዓመቱ ጊዜ የሚውል መሆኑም ተመልክቷል።
ካቢኔውም የቀረበለትን የበጀት ክለሳ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።
የክልሉ ካቢኔ ከዚህ በተጨማሪም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ አቅጣጫ ማስቀመጡን ኢዜአ ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘው መረጃ ያመለክታል።