ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ የአረንጓዴ የልማት አቅጣጫ በሁሉም ዘርፍ ዕድገትን የሚያፋጥን ስኬት እያስገኘ ነው

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 10/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የአረንጓዴ የልማት አቅጣጫ በሁሉም ዘርፍ ዕድገትን የሚያፋጥን ስኬት እያስገኘ መሆኑን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍስሀ ይታገሱ (ዶ/ር) ገለጹ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር በቂሊንጦ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ያስገነባውን ግዙፍ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ መሙያ ጣቢያ የምርቃት መርሀግብር በመካሄድ ላይ ነው።


 

በመርሀግብሩ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በርኦ ሀሰን፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር)፤ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ መሙያ ጣቢያው ወቅታዊ እና አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

ይህም ኢትዮጵያ እየተከተለችው ያለው የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ፖሊሲ አንዱ አካል መሆኑን ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ የአረንጓዴ የልማት አቅጣጫ በሁሉም ዘርፍ ዕድገትን የሚያፋጥን ስኬት እያስገኘ መሆኑንም አንስተዋል።

ከዚህም አንዱ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች መሆናቸውን ተናግረው፤ ወደፊት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ፍላጎት ለማሟላት ቻርጅ የማድረጊያ ጣቢያዎችን ማስፋት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በዛሬው እለት ለምረቃ የበቃው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ መሙያ ጣቢያ በወሳኝ ወቅት የመጣ እርምጃ መሆኑን አንስተዋል።


 

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ዋና መሪ ቃል አካባቢን የማይበክል አምራች ኢንዱስትሪ መሆኑንም በመግለጽ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ መሙያ ጣቢያው ከመሪ ቃሉ ጋር የተጣጣመ መሆኑን አንስተዋል።

ተቋማቱ ጥብቅ ቁርኝነት ያላቸው መሆኑን ገልጸው፤ በቀጣይም በትብብር እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም