የ“FAME by Sheeraz” መስራች ሺራዝ ሐሰን የአዲስ አበባን የቱሪዝም መዳረሻዎች ጎበኙ - ኢዜአ አማርኛ
የ“FAME by Sheeraz” መስራች ሺራዝ ሐሰን የአዲስ አበባን የቱሪዝም መዳረሻዎች ጎበኙ
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 9/2018 (ኢዜአ):- የ“FAME by Sheeraz” መስራች ሺራዝ ሐሰን እና ልዑካን ቡድናቸው በአዲስ አበባ የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎችን እና የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸውም የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማቶችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
የልዑካን ቡድኑ በአዲስ አበባ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች እንዲሁም የቱሪዝም መሠረተ ልማቶች ከተማዋ ተመራጭ የቱሪዝም ማዕከል እየሆነች መምጣቷን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።
“FAME by Sheeraz” የዲጂታል ሚዲያ እና የብራንዲንግ ድርጅት ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ ግለሰቦች እና ተቋማት ጋር በቅርበት የሚሰራ ተቋም መሆኑን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።