ፋሲል ከነማ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል - ኢዜአ አማርኛ
ፋሲል ከነማ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 8/2018 (ኢዜአ):- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ35ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ ሀዲያ ሆሳዕናን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው ጨዋታ ታምራት እያሱ በ43ኛው ደቂቃ ግቡን ከመረብ ላይ አገናኝቷል።
የፋሲል ከነማው ሀብታሙ ተከስተ በ38ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል።
ከሁለት ተከታታይ ሽንፈቶች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ፋሲል ከነማ በ49 ነጥብ ደረጃውን ከ10ኛ ወደ 5ኛ ከፍ አድርጓል። በሊጉም 12ኛ ድሉን አግኝቷል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 12ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሀዲያ ሆሳዕና በ43 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ቡድኑ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች ድል አልቀናውም።
ዛሬ ቀን ላይ በተደረጉ የ35ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች ነገሌ አርሲ ሃዋሳ ከተማን እና አዳማ ከተማ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን በተመሳሳይ 2 ለ 1 አሸንፈዋል።
አርባምንጭ ከተማ ምድረ ገነት ሽሬን 2 ለ 0 ረትቷል።