የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኮከብ ተጫዋች እጩዎች ይፋ ሆኑ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኮከብ ተጫዋች እጩዎች ይፋ ሆኑ
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 8/2018 (ኢዜአ):- የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኮከብ ተጫዋቾች ዝርዝር ዛሬ በሊጉ አክሲዮን ማህበር ይፋ ሆኗል።
በዚሁ መሰረት መስፍን ታፈሰ (ሲዳማ ቡና)፣ ዳዊት ተፈራ (ነገሌ አርሲ)፣ ያሬድ ባየህ (ሲዳማ ቡና) ፣ ቸርነት ጉግሳ (መቻል) ፣ አብዱልከሪም ወርቁ (መቻል) ፣ ናትናኤል ዳንኤል (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ፍፁም ጥላሁን (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ፍፁም አለሙ (መቀሌ 70 እንደርታ)፣ ሮሆቦት ሰላሎ (ነገሌ አርሴ) እና አቤል ያለው (ሲዳማ ቡና) በኮከብ ተጫዋች እጩነት ውስጥ ተካተዋል።
ሄኖክ ይበልጣል (ባህር ዳር ከተማ)፣ ሁዘይፋ ሻፊ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ከቤ ብዙነህ (ነገሌ አርሲ)፣ ያሬድ ብሩክ (ሃዋሳ ከተማ)፣ ሀብታሙ ጉልላት (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ዳዊት ካሳው (ሸገር ከተማ) እና ዳዊት አውላቸው (ኢትዮጵያ መድን) የኮከብ ተስፈኛ ተጫዋች እጩዎች ናቸው።
ደጋፊዎች በhttps://t.me/ethiopianlea የቴሌግራም ገጽ እስከ ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ድምጽ መስጠት እንደሚችሉ የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል።
ከተመልካቾች ድምጽ በተጨማሪ አሰልጣኞች፣ ጋዜጠኞችና የሊጉን ጨዋታ የቀጥታ ስርጭት መብት የወሰደው የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ የቴሌቪዥን ጣቢያ በድምጽ አሰጣጡ ድርሻ እንዳላቸው ተመላክቷል።
የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኮከብ ተጫዋቾች የሽልማት ስነ- ስርዓት የሚካሄድበት ጊዜ በቀጣይ ይፋ እንደሚደረግም ታውቋል።