የመውረድ ስጋት ያለበት አዳማ ከተማ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል - ኢዜአ አማርኛ
የመውረድ ስጋት ያለበት አዳማ ከተማ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 8/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ35ኛ ሳምንት መርሐ ግብር አዳማ ከተማ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 2 ለ 1 አሸንፏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አቡበከር ሳኒ እና አቤነዘር ሲሳይ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ናትናኤል ዳንኤል ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በፍጹም ቅጣት ምት ጎሏን አስቆጥሯል።
በሊጉ ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው አዳማ ከተማ በ42 ነጥብ ደረጃውን ከ16ኛ ወደ 15ኛ ከፍ አድርጓል። ከወራጅ ቀጠና በመጠኑ ፈቀቅ እንዲርቅ ያደረገውን ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል።
በውድድር ዓመቱም ዘጠነኛ ድሉን አስመዝግቧል።
በአንጻሩ በሊጉ 12ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ45 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንኩ ናትናኤል ዳንኤል በሊጉ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ብዛት ወደ 14 ከፍ በማድረግ ተመሳሳይ የግብ ብዛት ካለው የሲዳማ ቡናው አቤል ያለው ጋር የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን በጋራ መምራት ጀምሯል።