ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ - ኢዜአ አማርኛ
ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8/ 2018(ኢዜአ)፦ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡
ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው የተለያዩ ባህላዊ እና ሌሎች ይዘቶቸ ያሏቸው የሙዚቃ ሥራዎችን ለአድማጭ ተመልካች አበርክቷል፡፡
ድምጻዊው ለሕዝብ ካበረከታቸው የሙዚቃ ሥራዎች መካከል ነይ ዘመድዬ፣ እንዴት ነሽ፣ ደቦት እንስራ፣ ዘና በይ፣ ባላገር እና ሌሎች ይገኙበታል፡፡
ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ባለትዳር እና የአራት ልጆች አባት እንደነበር ኢዜአ ከቤተሰቦቹ ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለአድናቂዎቹ መጽናናትን ይመኛል፡፡