ቀጥታ፡

በክልሉ ከ97 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ክልል አቀፍ ፈተና እየተሰጠ ነው

ጂንካ፤ ሰኔ 8/2018 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከ97 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ክልል አቀፍ ፈተና እየተሰጠ ነው።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ታምራት ይገዙ (ዶ/ር) ዛሬ በጂንካ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት በተዘጋጀ የፈተና ማዕከል ተገኝተው ፈተናውን አስጀምረዋል።


 

ምክትል ቢሮ ኃላፊው እንደገለጹት፣ በክልሉ ከ97 ሺህ በላይ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ክልል አቀፍ ፈተናውን ዛሬ መውሰድ ጀምረዋል።

ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት በሚሰጠው በዚህ ፈተናም ተማሪዎች ወደቀጣይ ክፍል ለመሸጋገር ያላቸው ብቃት እንደሚመዘን ተናግረዋል። 


 

በተመሳሳይ ከሰኔ 11 እስከ 12 ቀን 2018 ዓ.ም በክልሉ ለሚገኙ 86 ሺህ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ክልላዊ ፈተና እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

በክልል አቀፍ ፈተናዎቹ በአጠቃላይ ከ180 ሺህ በላይ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱም ታምራት (ዶ/ር) አስታውቀዋል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም