ቀጥታ፡

‎የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በአፍሪካ ታሪክ ትልቁ የአቪዬሽን መሠረተ ልማት ፕሮጀክት ነው

አዲስ አበባ፤ሰኔ 8/2018(ኢዜአ) ፦ ‎የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በአፍሪካ ታሪክ ትልቁ የአቪዬሽን መሠረተ ልማት ፕሮጀክት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

ይህ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅም በዓመት 110 ሚሊዮን መንገደኞችን ለማስተናገድ እንደሚችል ገልጸዋል።


 

የፕሮጀክቶ መጠናቀቅ ኢትዮጵያን ከዓለም ቀዳሚ የአቪዬሽን ተርታ ለማሰለፍ የሚያስችል መሆኑን ገልጸው፥ ለዚህም ቀንና ሌሊት ባልተቋረጠ ቁርጠኝነት እየተገነባ ይገኛል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም