ቀጥታ፡

ኔዘርላንድስ እና ጃፓን አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 8 /2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ መርሐ ግብር ኔዘርላንድስ እና ጃፓን ሁለት አቻ ተለያይተዋል።

ማምሻውን በዳላስ ስታዲየም በተካሄደው የምድብ ስድስት የመጀመሪያ ጨዋታ ቨርጂል ቫን ዳይክ እና ክሬሴንሲዮ ሳመርቪል ለኔዘርላንድስ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ኬቶ ናካሙራ እና ዳቺ ካማዳ የጃፓንን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

የካማዳ የ88ኛ ደቂቃ ጎል ጃፓንን አቻ አድርጓል።

አራቱም ግቦች የተቆጠሩበት ሁለተኛ አጋማሽ የተሻለ እንቅስቃሴ ተደርጎበታል።

ሁለቱ ሀገራት በምድብ ስድስት የመጀመሪያ ነጥባቸውን አግኝተዋል።

በዚሁ ምድብ ስዊድን ከቱኒዚያ ከሌሊቱ 11 ሰዓት በሞንትሬይ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም