በአለም ዋንጫው አፍሪካዊቷ ኮትዲቯር ድል ቀንቷታል - ኢዜአ አማርኛ
በአለም ዋንጫው አፍሪካዊቷ ኮትዲቯር ድል ቀንቷታል
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 8/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የምድብ አምስት ሁለተኛ መርሐ ግብር ኮትዲቯር ኢኳዶርን 1 ለ 0 አሸንፋለች።
ከእኩለ ሌሊት በኋላ በፊላደልፊያ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ተቀይሮ የገባው አማድ ዲያሎ በ90ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።
አፍሪካዊቷ ኮትዲቯር በጨዋታው የተሻሉ የግብ እድሎችን ፈጥራለች።
የኳስ ቁጥጥር ብልጫ የነበራት ኢኳዶር አንድ ኢላማውን የጠበቀ የግብ ሙከራ ብቻ አድርጋለች።
ኮትዲቯር በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ድል ያስመዘገበች የመጀመሪዋ አፍካዊት ሀገር ሆናለች።
በዓለም ዋንጫው በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ 10 የአፍሪካ ሀገራት እየተሳተፉ ይገኛል።
በምድብ አምስት ትናንት በተደረገው ሌላኛው ጨዋታ ጀርመን ኩራሳኦን 7 ለ 1 አሸንፋለች።
በቀጣይ ጀርመን ከኮትዲቯር የሚያደርጉት የምድብ ጨዋታ ይጠበቃል።
ኢኳዶር ከኩራሳኦ ሌላኛው የምድቡ ሁለተኛ መርሐ ግብር ነው።