ቀጥታ፡

ስዊድን ቱኒዚያን 5 ለ 1 አሸንፋለች።

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 8/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የምድብ ስድስት ሁለተኛ ጨዋታ ስዊድን ቱኒዚያን 5 ለ 1 አሸንፋለች።

ማለዳ ላይ በተጠናቀቀው እና በሞንቴሬይ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ያሲን አያሪ (ሁለት) ፣ አሌክሳንደር ኢሳቅ፣ ቪክቶር ዮኮሬሽ እና ማቲያስ ስቫንበርግ የማሸነፊያ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ኦማር ረኪክ የቱኒዚያን ግብ አስቆጥሯል።

ቱኒዚያ በአንጻራዊነት የተሻለ የኳስ ቁጥጥር ቢኖራትም በበቂ ሁኔታ የግብ እድሎችን መፍጠር አልቻለችም።

ስዊድን በርካታ የግብ እድሎችን ፈጥራለች።

ውጤቱን ተከትሎ ስዊድን በሶስት ነጥብ ምድብ ስድስትን መምራት ጀምራለች።

ቱኒዚያ ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛለች።

በዚሁ ምድብ ትናንት በተደረገው ሌላኛው ጨዋታ ኔዘርላንድስ እና ጃፓን ሁለት አቻ ተለያይተዋል።

ቱኒዚያ ከጃፓን፣ ስዊድን ከኔዘርላንድስ በምድብ ስድስት የሚደረጉ ቀጣይ መርሐ ግብሮች ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም