የአፍሪካ አገራት ተሳትፎ በከፍተኛ ሁኔታ ያደገበት የዓለም ዋንጫ - ኢዜአ አማርኛ
የአፍሪካ አገራት ተሳትፎ በከፍተኛ ሁኔታ ያደገበት የዓለም ዋንጫ
አዲሱ የ48 ቡድኖች ተሳትፎ ከጠቀማቸው አህጉራት መካከል አፍሪካ አንዱ ነው።
ቀደም ሲል ለአፍሪካ ይሰጥ የነበረው ቦታ አምስት ብቻ የነበረ ሲሆን፣ በዚኛው ውድድር ግን ዘጠኝ ሀገራት በቀጥታ የመሳተፍ እድል አግኝተዋል።
በዚህም መሰረት ሞሮኮ፣ ሴኔጋል፣ ግብፅ፣ ኮትዲቯር፣ አልጄሪያ፣ ቱኒዚያ፣ ጋና፣ ኬፕቨርዴ እና ደቡብ አፍሪካ በቀጥታ ያለፉ የአፍሪካ ሀገራት ናቸው።
በአንጻሩ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ብሔራዊ ቡድን በክፍለ አህጉራዊ አህጉር አቋራጭ የማጣሪያ ውድድር (Play-off) የጃማይካን አቻውን በመርታት ለዓለም ዋንጫው ያለፈች 10ኛዋ የአፍሪካ ሀገር በመሆን አዲስ ታሪክ ሰርታለች።