በተጠባቂው ጨዋታ ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ቡናን 2 ለ 1 አሸንፏል - ኢዜአ አማርኛ
በተጠባቂው ጨዋታ ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ቡናን 2 ለ 1 አሸንፏል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7 /2018 (ኢዜአ)፦ በተጠባቂው የ35ኛ ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ጨዋታ ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ቡናን 2 ለ 1 አሸንፏል፡
ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ቡናን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡
ለሲዳማ ቡና የማሸነፊያ ግቦቹን ያሬድ ባየህ እና ብርሃኑ በቀለ ሲያስቆጥሩ፥ ኢትዮጵያ ቡናን ከሽንፈት ያልታደገች ግብ ዘላለም አባተ ከመረብ አሳርፏል፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ሌላኛው የዕለቱ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ መቻልን 3 ለ 0 ሲያሸንፍ ፍፁም ጥላሁን፣ ሀብታሙ ጉልላት እና የአብስራ ጎሳዬ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡